Cabu Liquor Store - ካቡ መጠጥ ማከፋፈያ

Cabu Liquor Store - ካቡ መጠጥ ማከፋፈያ

Share

Iiquer store

17/12/2025
Photos from Cabu Liquor Store - ካቡ መጠጥ ማከፋፈያ's post 20/11/2024
29/01/2024

ጥምቀትን እንዲህ አክብረናል እናንተስ ፣?

20/08/2023

የድሮ ስልክዎን የሚጠቀሙበት 5 መንገዶች
በቤቶ የማይጠቀሙበት ሞባይል ስልክ ካልዎት ለነዚህ ጠቃሚ ተግባሮች ያውሉት።

ይህ መረጃ ይጠቅማቸዋል ለሚሏቸው ሰዎች ሼር በማድረግ ላይክ በማድረግ እንዲሁም የሰዎችን የፌስቡክ ስም ኮመንት ላይ በማስቀመጥ እንዲደርሳቸው ያድርጉልን።

1. የደህንነት ካሜራ ወይንም CCTV
የደህንነት ካሜራ ማስቀመጥ ፈልገዋል መጀመሪያ ስልክዎን ለመጠቀም ይሞክሩ ይሄንን ለመጠቀም (Google Play Store) ላይ (Alfred Home Security Camera) የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን በማውረድ ድሮ ስልክዎን ከአዲሱ ስልክዎ ጋር በማገናኘትና የድሮ ስልክዎን የሚፈልጉት ቦታ ላይ በማስቀመጥ ያለማቋረጥ የአካባቢውን ሁኔታ መከታተል ይችላሉ። ምስሉ እንዳይቋረጥ ከኢንተርኔት ጋር ማገናኘትና ቻርጅ መሰካት ብቻ በቂ ነው።
2. ጂፒኤስ መከታተያ (GPS Tracker)
አዎ የማይጠቀሙበት ስልክ ምንም ቢያረጅም በላዩ ላይ የቦታ ማወቂያ (GPS Tracker) ያለው ነው። ይሄም በመሆኑ ነባር ስልካችንን በመከታተል ለምሳሌ መኪናችንን መከታተል እንችላለን። ይሄንንም እንደ Life360 ወይንም የራሱ የጉግልን (Find My Device) በመጠቀምና ከአዲሱ ስልካችን ጋር በማገናኘት መኪና ያለበትን ቦታ መከታተል እንችላለን። በዚህ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የምትፈልጉ ከሆነ ኮመንት ቦታ ላይ (2 ማብራሪያ) ብለው ይጻፉልን በቀጣይ ማብራሪያ ይዘን እንመጣለን።
3. የመኪና ካሜራ (Dash Cam)
አዲስ የመኪና ካሜራ (Dash Cam) ከመግዛትዎ በፊት ነባር ስልክዎን ቢሞክሩት አስገራሚ ውጤት ሊያገኙበት ይችላሉ። ስልካችን ቪዲዮ መቅረጽ ስለሚችል ረጅም ሰዓት ለመቅረጽ ተለቅ ያለ ሜሞሪ በማስገባት ወይንም የሚቀርጽበትን ጥራት በመቀነስ ሙሉ ቀን የመኪናችንን እንቅስቃሴ መቅረጽ እንችላለን። ይሄ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር በምናሽከረክርበት ጊዜ የሚፈጠር ማንኛውንም ድንገተኛ ነገር ማስረጃ ለመያዝ ያስችለናል።
4. እንደ ሁለተኛ ፋይል ማስቀመጫ (Backup Storage)
ስልካችን ቢጠፋ ወይንም በተለያየ ምክንያት ከጥቅም ውጪ ቢሆን የስልካችንን ሙሉ መረጃ ነባሩ ስልካችን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን። (Google Drive) የመሳሰሉት አገልግሎቶች መጠቀም እንችላለን ነገር ግን የምናስቀምጠው ነገር መጠን ውስንነት ስላለው አሮጌ ስልካችንን እንደ አማራጭ መተቀም እንችላለን። ይሄንን በቀላሉ ለመጠቀም እንደ Resilio Sync ያሉ መተግበሪያዎችን በማውረድ እና ሁለቱም ስልክ ላይ በመጫን ከዛም ከኢንተርኔት ጋር በማገናኘት ሙሉ መረጃችንን በአሮጌው ስልክ ላይ ማስቀመጥ ያስችለናል።
5. ከነዚህ በተጨማሪም
ነባር ስላችንን ከ ስፒከር ጋር በማገናኘት እንደ ሙዚቃ ማጫወቻ ልንጠቀመው እንችላለን። እንዲሁም እንደ ቲቪ ሪሞት ኮንትሮል ልንጠቀመው እንችላለን።
በይስሀቅ ግርማ

19/06/2023

የጣሪያና ግድግዳ ግብርን በተመለከተ ለግንዛቤ
ክፍል-2
------
በተለምዶ የጣሪያና ግድግዳ ግብር እየተባለ የሚታወቀው የቤት ግብር በአገራችን ከ1937 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን በዋናነት በከተማ ማዘጋጃ ቤቶች እየተሰበሰበ ተመልሶ ለከተሞች ልማት ሲውል ቆይቷል።

ይህ የገቢ ምንጭ የሚሰላበት ሁኔታ መሠረት የሚያደርገው በአመታዊ የቤት ኪራይ ግምት ላይ ተመስርቶ የሚሰላ መሆኑን አሁን በሥራ ላይ ባለው የቦታ ኪራይ እና ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በተሻሻለው ማቋቋሚያ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 መሰረት ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች ገቢ እንዲሰበስብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከመሬት ኪራይና ከቤት ግብር (ጣሪያና ግድግዳ) በሚል የንብረት ባለቤቶች እንዲከፍሉ ሲደረግ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየጨመረ ከመጣው የከተማው ህዝብ ብዛት ጋር ተያይዞ እና እያደገ ከመጣው የህዝብ የአገልግሎት ፍላጎት እና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ከተማው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ መሰብሰብ ይጠበቅበታል።

በከተማ አስተዳደሩ ማቋቋሚያ ቻርተር ላይ ስልጣን ከተሰጠው የገቢ ዓይነቶች አንዱ የቤት ግብር ነው። ይሁን እንጂ በስራ ላይ ባለው የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ስርዓቱ ያልዘመነ ከመሆኑ በላይ ከተማው ከዚህ ዘርፍ የሚሰበስበው ገቢ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

ስለሆነም አሁን ያለው ዓመታዊ የቤት የኪራይ ግምት አገልግሎቱን ለመስጠት የሚወጣው ወጪ የማይሸፍን እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ፣ ሳይሻሻልም ለረጅም ዓመታት የቆየ፣ ከግዜው ጋር መዘመን የማይታይበት መሆኑን በመገንዘብ የዓመታዊ ኪራይ ዋጋ ተመን ወቅታዊ ተደርጓል።

የተደረገው ማሻሻያ ምንድን ነው..??
-------
የማዘጋጃቤታዊ ገቢን ለማሳደግ የተጻፉ ጹሁፎችና ጥናቶች እንደሚያስረዱት አንድ ከተማ አስተዳደር የሚሰጠውን አገልግሎቶች ለማስፋፋት እና እያደገ የመጣውን የነዋሪዎች ፍላጎት ለማሟላት የገቢ ምንጮችን ማስፋትና የክፍያ ተመንን ወቅታዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ነው።

ስለሆነም በአጭርና በረዥም ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ የሚፈልጉ ተመኖችን ለይቶ ጥናት በማድረግ ገቢን ማሳደግ እንደሚጠበቅ ያስቀምጣሉ።

የቤት ግብር (የጣሪያና ግድግዳ ግብር) አሁን በስራ ላይ ያለውን ህግ ማሻሻል ሳያስፈልግ ግብር ለመወሰን እና ለመሰባሰብ የሚያስችሉ ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግ ከዘርፉ የሚሰበሰበውን ሀብት ማሳደግ ይቻላል።

በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በስራ ላይ ያለውን ከቤት ግብር የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የግብር ከፋዩን ህብረተሰብ አቅም ያገናዘበ፣ የመሰረተ ልማት ጥያቄን የሚመልስና የገንዘብ መግዛት አቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊተገበር የሚችለው የግብር ማሻሻ እንደሚከተለው ቀርቧል:-

(1ኛ). በቤቱ ላይ የሚጣለው ግብር መጠን የሚወሰነው በሚገኘው አመታዊ ቤት ኪራይ ሲሆን የህንጻው ዓይነት፣ የህንጻው ስፋት፣ የአካባቢው የማከራያ ዋጋ እና ቤቱ ያለበታ ቦታ ደረጃ ግብር ለመወሰን ወሳኝ ግብዓቶች በመሆናቸው የቤት ግብር የሚከፈልባቸው ህንጻዎች ለቤት ግብር አወሳሰን እና አስተዳደራዊ ቅለት ሲባል የቤት ዓይነቶች በ3 ምድብ እንዲከፈሉ ተደርጓል፡፡

ሀ. ከእንጨት እና ከጭቃ የተሰሩ ቤቶች
ለ. የኮንደሚኒየም ቤቶች
ሐ. ቪላ (ከብሎኬት የተሰሩ) አፓርታማ እና ተመሳሳይ ህንጻዎች ናቸው።

(2ኛ).በህንጻ አጠቃቀማቸው ወይም በአገልግሎት ዓይነታቸው ደግሞ
ሀ. የመኖሪያ እና
ለ. የንግድ (የድርጅት) በሚል በሁለት እንዲከፈሉ ተደርጓል።

(3ኛ).የቦታ ደረጃን በተመለከተ ለአሰራር ቅለት ደረጃ 3 እና ደረጃ 4 በአንድ ላይ በመቀላቀል በሶስት የቦታ ደረጃ በመክፈል የተሰራ ሲሆን ይህም:-
ሀ. ደረጃ 1
ለ. ደረጃ 2
ሐ. ደረጃ 3 እና ደረጃ 4 ናቸው።

(3ኛ). የንብረት ግመታና የግብር ስሌትን በተመለከተ በኮምፒውተር የሚቀነባበር የንብረት ግብር ሥርዓት ተደራጅቶ ሥራ ላይ እስኪውል ድረስ በስራ ላይ ያለው አካባቢ ተኮር የሆነው የቤት ግብር ትመና በየዓመታዊ የኪራይ ዋጋ የገበያ ጥናት በማድረግ ተሻሽሎ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ስሌቱም፡- የቤት ግብር = የህንጻ ስፋት × ለቦታ ደረጃው የተሰጠው አማካኝ ዓመታዊ የኪራይ ዋጋ × በግብር መጣኔው
----
በመመሪያው አተገባበር ሂደት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ:-
=>> የቤት ግምት ወይም ዓመታዊ የቤት ኪራይ ዋጋ ለማስላት ወጥቶ በባለሙያ መለካት ያስፈልጋል ወይ?
---
> የቤት ግምት ወይም ዓመታዊ የቤት ኪራይ ዋጋ ለማስላት የምንጠቀምበት መረጃ በተመለከተ ለእያንዳንዱ ቤት ወጥቶ አሁን መለካት የማያስፈልግ ሲሆን በቀጣይ በኦዲት የሚረጋገጥ በመሆኑ ከዚህ በታች በተመለከተው ቅደም ተከተል መሰረት ተግባራዊ ማድረግ አለበት።

> መጀመሪያው አማራጭ በመሬት ተቋማት የተሟላ መረጃ ካለን የቤቱን ስፋት፣የቦታ ደረጃውንና የአገልግሎት ዓይነት በመውሰድ መወሰን፣
> ሁለተኛው አማራጭ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሰበሰበ መረጃን በመጠቀም መወሰን፣
> ሶስተኛው አማራጭ ባለ ንብረቶች (ግብር ከፋዮች)የቦታውን ልዩ መጠሪያ የቤቱን ስፋት እና የአገልግሎቱን ዓይነት በፊርማቸው አረጋግጠው እንዲያሳውቁ (self-declare) በማድረግ በቀረበው መረጃ መሰረት ለቦታ ደረጃው እና ለቤቱ ዓይነት በተወሰነው መሰረት ዓመታዊ የንብረት (የቤት)ግብር በማስላት ለገቢዎች ማሳወቅ።

=>> የአንድ ሰው ይዞታ ስር የተገነባ ቤት ከጭቃ ወይም እንጨት እና ከብሎኬት ቤት ቢኖሩት የአመታዊ የኪራይ ዋጋ ግምቱ በየትኛው ይሰላል?
---
> የአንድ ሰው ይዞታ ስር የተገነባ ቤት ከጭቃ ወይም እንጨት እና ከብሎኬት ቤት ቢኖሩት የአመታዊ የኪራይ ዋጋ ግምቱ በየትኛው ይሰላል የሚለውን በተመለከተ ከጭቃ ወይም በዝቅተኛው እንዲሰራ እንዲሁም በቆርቆሮ የተሰራ ቤት በጭቃ እንዲሁም በብረት(በላሜራ) የተሰራ በብሎኬት ስሌት መሰራት አለበት።

=>> ቅሬታ እንዴት ማቅረብ ይቻላል?
---
> በክፍለ ከተማ ደረጃ ቅሬታ አለኝ የሚል ማንኛውም ግብር ከፋይ ቅሬታውን ማቅረብ ይቻላል፡፡

=>> ጅምር ቤቶች እንዴት ይገመታሉ?
---
ጅምር ቤቶች በተመለከተ ግንባታቸው በደረሰበት ደረጃ ሆኖ በተጠናቀቀው እና ለአገልግሎት ዝግጁ በሆነው መጠን ግብር የሚከፈልባቸው ይሆናል።

=>> የቦታ ደረጃው ግልጽ አይደለም..
---
የቦታ ደረጃውን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠንቶ በ2014 ተግባራዊ የተደረገውን መሠረት የሚገመት ይሆናል።

ይህ የሚታወቀው በካርተው ላይ ያለውን X,Y coordinate ወይም የቦታውን ልዩ የሰፈር መጠሪያ በመጠቀም የቦታ ደረጃውን ማወቅ ይቻላል፡፡

=>> ሰነድ አልባ ቤቶች ግብር ይከፍላሉ ወይ...?
---
ሰነድ አልባ ቤቶችን በተመለከተ ይዞታውን የማረጋገጥ ሥራ ቅድሚያ መተግበር የሚገባው ተግባር ሆኖ መብት ያልተፈጠረለትን የቤት ግብር ማስከፈል አይቻልም።

=>> በካርታ ላይ የተገለጸ የይዞታ መጠቀሚያ ለመኖሪያ ሆኖ ሳለ ለሥራ እየተጠቀሙ ለሚገኙ ሰዎች የቤት ኪራይ ግምቱ በየትኛው አገልግሎት ይሰላል..?
---
በካርታ ላይ የተገለጸ የይዞታ መጠቀሚያ ለመኖሪያ ሆኖ ሳለ ለሥራ እየተጠቀሙ ለሚገኙ ሰዎች የቤት ኪራይ ግምቱ በየትኛው አገልግሎት ይሰላል ለሚለው በካርታ ላይ ባለው እንዲሰላ ይደረጋል።

=>> አጠቃላይ የ2015 ግብር ዘመን መክፈል የሚገባቸው ግብር ከፋዮች እነማን ናቸው?
---
የ2015 ግብር ዘመን መክፈል የሚገባቸው ግብር ከፋዮች እስከ የካቲት 30/2015 ድረስ ያልከፈሉ እና አስካሁን ወደ ግብር ስርዓቱ ያልገቡ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ሁሉም ግብር ከፋዮች በማሻሻያው መሰረት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

=>> የማህደር ማጣራት እና የመሃንዲስ ክፍያ ለምን እንከፍላለን?
---
የማህደር ማጣራት እና የመሃንዲስ ክፍያ በተመለከተ አሁን የተደረገው የንብረት ግብር አተገባበር በብዘሃ ግመታ (Mass Valuation) የሚተገበር በመሆኑ የማህደር ማጣራት እና የመሃንዲስ ክፍያ መጠየቁ በግብር ከፋዩ ላይ ጫና መፍጠር እና ስራውንም ስለሚያጓትት በነጻ አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

=>> አንድ ሰው ለመኖሪያ እና ለሥራ (ለቅይጥ) አገልግሎት ለሚጠቀመው ቤት የአመታዊ የኪራይ ዋጋ ግምቱ እንዴት ይሰላል?
---
አንድ ሰው ለመኖሪያ እና ለሥራ (ለቅይጥ) አገልግሎት ለሚጠቀመው ቤት የአመታዊ የኪራይ ዋጋ ግምቱ በተመለከተ በአንድ ግቢ ውስጥ ለመኖሪያ እና ለሥራ የሚጠቀም ግብር ከፋይ ቢያጋጥመን ለመኖሪያ የተጠቀሙት ጠቅላላ የቤት ስፋትን በመኖሪያ ቤት ዋጋ በማባዛት እና ለስራ የሚጠቀሙበትን ጠቅላላ የቤት ስፋትን ለሥራ በተጠናው የቤት ኪራይ ዋጋ በማባዛት በመጨረሻም ሁለቱን በመደመር የቤት ኪራይ ዋጋውን በማግኘት የሚሰላ እንደሚሆን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Photos from ASER MEDIA's post 26/03/2023
14/06/2022

አንስታይን
ሙሉውን የአንስታይን የህይወት መርዎች በዚህ ሊንክ ይመልከቱ

https://youtu.be/UgWOT4xYQUE

Want your business to be the top-listed Furniture Store in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

የካ አባዶ ኮንደምኒየም ጂ 7 ከነማ አካባቢ
Addis Ababa