14/06/2025
Jummi miirhagdeetti!
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from investinjimma.com, Jimma City Administration, Jimma.
14/06/2025
Jummi miirhagdeetti!
14/06/2025
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን !
ዛሬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን ከአንበሳ ጋራዥ_ጃክሮስ እና የጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አድርገናቸዋል ።
ይህ መስመር የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ የሚታይበት ለአደጋ የተጋለጠና አስቸጋሪ መስመር ነበር።
አሁን ደረጃውን የጠበቀ አስፖልት ፣ የእግርኛ መንገድ እና የብስክሌት መስመር ፣ የህፃናት መጫዎቻ ፤ የመኪና ፓርኪንግ ፣ታክሲ እና አዉቶቢስ መጫኛና ማዉረጃ ፣የህዝብ ማረፊያ ክፍት ቦታዎች፣የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች እና የንግድ ቤቶች ከመንገድ ዳር ያላቸው ርቀት ታሳቢ ተደርጎ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ አካታች መሰረተ ልማት ያካተቱ ናቸዉ።
ከጎሮ ዋና መስመር ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች እና ከቦሌ አለም አቀፍ የበረራ ጣቢያ በኩል የሚመጡ ተሸከርካሪዎችን በማስተንፈስ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ መፍትሔ ይሰጣል።
በተጨማሪም ሰፊ የንግድ ስራዎች እንዲፈጠሩ በማስቻል በሺዎች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ነዉ።
ሁሌም ህዝብን መሠረት ያደረገ ልማት መስራታችን ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ የምናስረክባት አዲስ አበባ ፅዱ፣ ውብ አበባ እና ለመኖር ምቹ ለጐብኝዎች ተመራጭ እስከምትሆን ሌት ተቀን መትጋታችንን አጠናክረና እንቀጥላለን።
በኮሪደር ልማቱ መስመር የተካተቱ ስራዎች ፦
4ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ ፤ ከ8 ኪሎ ሜትር በላይ ደረጀውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ ፤
3 የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ቦታዎች ፣ የህፃናት መጫዎቻዎች ፣ 7 ፕላዛዎች ፣ 6 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ፣ ፋውንቴኖች 13 ታክሲ መጫኛና ማዉረጃ እና 872 ሱቆች ይገኙበታል ::
ዉድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን የልማት ስራ አጠናቀን እነሆ ስንላችሁ የናንተ መሆኑን በመረዳት እየጠበቃችሁት እንድትጠቀሙበት እያልኩ ለነበራችሁ ድጋፍ ፣ ላደረጋችሁት ትብብር እና ተሳትፎ ምስጋናዬን በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
Waaqni nu gargaare haa galatoomu!
Har'a kabajamoo Muummicha ministeeraa keenya Dr.Abiy Ahimad waliin ta'uun hojiiwwan misooma koriidarii Garaazhii Anbassaa irraa hanga Addabaabaayii Gooroo daaw'annee tajaajila uummataaf banaa taasisnee jirra.
Sararri kuni dhiphinni tiraafikaa kan itti mul'atuu fi balaaf saaxilamaa ture. Sarara rakkisaa ture. Amma asfaaltii sadarkaasaa eeggate,daandii miilaa fi sarara biskeeleetii,bakkeewwan daa'imman itti xaphatan,paarkiingii konkolaataa,bakka fe'uumsaa fi buusaa taaxsii fi baasii, bakkeewwan banaa haara galfannaa uummataa,manneen qulqullina uummataa fi manneen daldalaa fageenyi daandii irraa qaban ilaalcha keessa galamee fayyadamummaa kutaa hawaasaa hunda ilaalcha keessa kan galche bu'uura misoomaa hunda hammateedha.
Konkolaattotaa Sarara guddaa gooroo irraa dhufanii fi karaa waajjira balallii idil-addnuyaa Booleetiin dhufan furuun dhiphina tiraafika magaalaaf furmaata ni kenna.
Dabalataanis hojiiwwan daldalaa bal'aan akka uumaman dandeessisuun jiraattota kumaatamaan lakkaa'amaniif carraa hojii dhaabbataa kan uumeedha. Yeroo hundaa misooma uummata bu'uura godhate hojjechuu qofaa osoo hin taane Finfinneen dhalootaaf dabarsinu qulqullooftuu, abaaboo miidhagduu fi jireenyaaf mijattuu, daaw'attootaaf filatamtuu haga taatutti halkanii fi guyyaa hojjechuu keenya cimsinee itti fufna.
Hojiiwwan sarara misooma koriidarichaa keessatti hammataman:-
Daandii biskeeliitii 4km, sadarkaa isaa kan eeggate daandii miilaa 8Km oli, bakkeewwan paarkiingii konkolaattonni dhaabbatan 3, Bakkeewwan daa'imman itti xaphatan,Pilaazota 7,Manneen qulquillina uummataa 6,Faawunteeniilee, bakka fe'uumsaa fi buusaa taxsiilee 13 fi suuqiileen 872 keessatti argamu.
Qaaliiwwan jiraattota magaalaa keenyaa hojii misoomaa kana xumurree kunoo wayita isiniin jennu keessan ta'uu hubachuun kunuunsaa akka itti fayyadamtan isiniin jechaa deeggarsa qabaattaniif,tumsaa fi hirmaannaa taasistaniif maqaa bulchiinsa magaalaatiin galata koo isiniif dhiheessuun barbaada.
Waaqni Itoophiyaa fi Uummataa Ishee Haa Eebbisu!.
14/06/2025
09/12/2024
08/12/2024
30/10/2024
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጽ/ቤት በአካል በመገኘት የምስጋና ሥጦታ በክብር አበርክቷል፡፡
===============================
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ሸኽ አብዱልሃሚድ አህመድ፣ የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የማኔጅመንት አባላት፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ተቋሙ ላበረከተው ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የምስጋና ስጦታ በክበር አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሚሰራው የሰላም ግንባታ ሥራ የተሳካ እንዲሆን ቢሮ በማመቻቸት እንዲሁም ተዛማጅ አገልግሎቶች በመስጠት እና ድጋፎችን በማድረግ ላበረከተው የላቀ አስተዋጻኦ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በተያያዘም የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑትን አሮጌ ሕንፃዎች ለእይታ በሚያምር መልኩ፣ ለሥራ እና ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ በማድረግ፣ እንዲሁም አዳዲስ ታላላቅ ሕንፃዎችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ በራስ አቅም በመገንባታ ለሃገር ሃብት ከመፍጠር አንፃር የሰሩት ሥራ እጅግ የሚያኮራ እና ለሌሎች ተቋማትም ምሳሌ የሚሆን ሥራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በበኩላቸው ለተቋሙ ለተበረከተው የምስጋና ስጦታ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮችን ከልብ አመስግነዋል፡፡
አክለውም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ሰላምን ለማስፈን፣ በሕዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር እየሰራው ያለውን ሥራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም ተቋማተ የልማት ሥራን ባቀዱት ልክ መሥራት እና ማሳካት ይችሉ ዘንድ ሰላም እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተያያዘም አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም በሃገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን ጥረት ከሚያደርጉት ዋና ዋና ተቋማት ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመሆኑ ጉባኤውን መደገፍ ሰላምን መደገፍ ነው እንዲሁም የሰላም መስፈን ፋይዳው ለመላው የሃገሪቱ ሕዝብ በመሆኑ ጉባኤውን አቅም በፈቀደ ሁሉ መደገፍ ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል፡፡
Federal Housing Corporation - Ethiopia Housing Corporation - Ethiopia
30/10/2024