07/09/2026
መልካም የሥራ ሳምንት!
🌼🌼 🌼🌼
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
Interest Free Banking (CBE NOOR) The history of Commercial Bank of Ethiopia (CBE) dates back to the establishment of the State Bank of Ethiopia in 1942.
CBE was legally established as a share company in 1963. Since then, it has been playing significant roles in the development of the country. Currently CBE has more than 38.9 million account holders in its more than 1879 branches and the number of Mobile and Internet Banking users also reached more than 6 million and 39K. Active ATM card holders reached more than 8.8 million and 17 million CBE Birr users.
07/09/2026
መልካም የሥራ ሳምንት!
🌼🌼 🌼🌼
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
06/09/2026
“አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት የ2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ኢሮፕ ወረዳ ደዉሃን ከተማ በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ ለተጎዱ 230 ወገኖች ማዕድ አጋራ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የመቐለ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ልሳነወርቅ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ፤ ባንካችን የ2019 ዓ/ም አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ይህንን ድጋፍ ሲያደርግ የመጀመሪያዉ ሳይሆን ባለፉት ዓመታትም በተለያዩ አከባቢዎች መሰል ድጋፍ ሲያደርግ ቆይተዋል ።
በዚህ ዓመት ደግሞ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ኢሮፕ ወረዳ በደዉሃን ከተማ ተገኝተን ለ230 ወገኖች አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን እነደዚህ ዓይነት ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ። አቶ ኤልያስ ልሳነውርቅ ድጋፍ ለተደረገላቸዉ ወገኖች ሁሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችዉ በመመኘት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁል ጊዜ ከጎናችሁ ሆኖ ማህበራዊ ሓላፊነቱን በመወጣት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል አደጋ ስጋትና ቅድም ዝግጁነት ኮምሽን ኮሚሽንር ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሰራተኞቹ ሁል ጊዜ ከጎናችን ሆነዉ በየዓመቱ ድጋፍ ሲያደርጉልን ቆይተዋል ። በዚህ ዓመት የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ በኢሮፕ ወረዳ ደዉሃን ከተማ መደረጉ ደግሞ በአከባቢዉ ያለዉ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያስገባ እና ወቅታዊ ድጋፍ ነዉ ብለዋል ። ለባንኩ ያላቸዉ ምስገናም ትልቅ መሆኑን ገልጸዉ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል ።
የኢሮፕ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢያሱ ምስግና በበኩላችዉ ፤ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያላችዉ ምስጋና የላቀ መሆኑን በመግለጽ በጣም ረዥም ጉዞ በመጓዝ በደዉሃን ከተማ ለሚገኙ 230 ወግኖች ለአዲስ ዓመት በዓል ማሳለፍያ የሚሆን የማዕድ ማጋራት ድጋፍ መደረጉ በወረዳዉ አስተዳደር ስም እና በማህበረሰቡ ስም ከልብ አመስግነዋል ።
የትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ ካሕሳይ ገ/ስላሴ በማ|ዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ እንደገልጹት ፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተደርገው ድጋፍ ለአከባቢዉ ማህበረሰብ በጣም ወሳኝ ነዉ ብለዋል። አከባቢዉ ባለዉ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ብዙ ጊዜ በድርቅ የሚጠቃ አከባቢ ስለሆነ ድጋፉ ወቅቱን ያገናዘበ እና በወሳኝ ስዓት የቀረበ ድጋፍ ነዉ ብለዋል። የዞኑ አስተዳደርም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለዉ ምስጋና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች ፤ የዓዲ-ግራት እና የኢሮፕ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የአካባቢዉ የሃይማኖት አባቶችም ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸዉ አቅርበዋል።
06/09/2026
የወደቁትን ማንሳት እና ፣ ሕይወትን ማዳን — የጋራ ተልዕኮ!
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ሰው ተኮር ተልዕኮውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።
*************
በፕሬዚዳንቱ የተመራ የባንካችን የሥራ መሪዎች በአዲስ አበባ አያት 49 የሚገኘውን የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ጎብኝቶ፣ ማህበሩ በማስገንባት ላይ ያለውን ሕንፃና ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተመልክቷል።
አቶ አቤ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ መቄዶንያ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የምያከናውነው ሰው ተኮር ተግባር ከፍተኛ ማህበራዊ እሴት አለው።
ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የባንኩ ሰራተኞችና የሥራ መሪዎች ከመቄዶንያ ጎን እንደቀድሞው ሁሉ በመቆም ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው፣ “ከብዙ ማህበራዊ ጉዳዮች መቄዶንያን በማስቀደም በእረፍት ቀናችሁ ስለጎበኛችሁን እናመሰግናለን” በማለት ለባንኩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ቢኒያም እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የባንኩ ሰራተኞች በየጊዜው የሚያደርጉት ድጋፍና ጉብኝት ለማህበሩ የሥራ አቅም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው።
ማህበሩ ጳጉሜን 1ን “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀን” ብሎ መሰየሙንም አስታውሰዋል።
በመገባደድ ላይ ያለው የማህበሩ ሕንፃም ሆነ በማህበሩ የሚከናወኑት የበጎ አድራጎት ሥራዎች የባንኩን ጨምሮ የተለያዩ ቅን አሳቢ ተቋማትና ዜጎች ያደረጉት የጋራ ድጋፍ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
06/09/2026
“አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክ መጭውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ለ200 አቅመ ደካማዎች የማዕድ ማጋራት መርሃ -ግብር ድጋፍ አደረገ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ዛሬ በተካሄደው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ አፈወርቅ ሰንደቁን ጨምሮ፤ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ ዋለ፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ ሽባበው፣ የባንኩ የስራ ሃላፊዎች፣ የከተማዋ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች ተገኝተዋል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ ፣"አዲስ ዓመት በአገልጋይነት እና በጎነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ ለ 200 ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ለእያንዳንዳቸው የ በባዕል መዋያ የሚሆን የዳቦ ዱቄት፣ ዘይትና የኪስ ገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
ድጋፉን ያገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግራቸውን በመገንዘብ ከጎናቸው በመቆሙ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
06/09/2026
ጳጉሜ ወርን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሳለፍ መጪውን አዲስ ዓመት በንቃት መቀበል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ጳጉሜ ወርን ምክንያት በማድረግ በዋናው መስሪያ ቤት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄዱ።
********
በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንካችን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ በባንካችን በየዓመቱ በጳጉሜ ወር የሚካሄደው ስፖርታዊ ሁነት፤ ጤናን ለመጠበቅና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል ከማድረግ ባሻገር መጪውን አዲስ ዓመት በንቃት ለመቀበል እንዲያስችል መሆኑን ተገልፀዋል፡፡
የባንካችን የጤና እና ዌልነስ ዩኒት ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አለማየሁ በበኩላቸው የባንኩ ሰራተኞች ንቁ እና ጤናማ እንዲሆኑ በባንኩ ዋናው መ/ቤት፣ በዛጉዌ እና ህዳሴ ህንፃ ላይ ባሉት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዕከላት አማካኝነት የባንካችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር በሠራተኞች መካከል ጥብቅ ትስስርን በመፍጠር አንድነትን እና አብሮነትን እያጠናከረ የመጣ ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል።፡
በተጨማሪም የ2018 ዓ.ም ሸኝተን አዲሱን 2019 ዓ.ም የምንቀበልበትን የጳጉሜ ወር አምስቱን ቀን “ጤናማ ሠራተኛ ውጤታማ ሰራተኛ ነው” በሚል የማስ ስፖርት መርሃ ግብር በመጀመር መጪውን አዲስ ዓመት በንቃት፣ በጤንነት ብሎም በበለጠ በአገልጋይነት እንድንቀበለው እና የዘላቂ ጤናማ አኗኗር መጀመሪያ መሆኑን ቃል የምንገባበት ወርም ጭምር ነው ሲሉ አቶ ያሬድ ተናግረዋል።
ጳጉሜ 1 ቀን በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት የተጀመረው ይህ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን፤ በየቀኑ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የባንኩ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
05/09/2026
“አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት የ2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ240 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ።
**********
የደሴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሰይድ አሊ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ሀገር ታላላቅ የሀገር የልማት ፕሮጀክቶችን በዋናነት ፋይናንስ ከማድረግ ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በቀዳሚነት እየተወጣ የሚገኝ የማህብረሰቡ የቅርብ አጋር መሆኑን በመግለፅ፤ ባንካችን በ2019 አዲስ ዓመት የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በሁሉም ዲስትሪክቶቻችን አማካኝነት በድምሩ ከ6,600 በላይ ለሚሆኑ ድጋፍ የሚያሻቸው ወገኖቻችን ‘አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት' በሚል መሪ ቃል ማዕድ በማጋራት ላይ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን እንደ ደሴ ድስትሪክት ከ240 በላይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያና የደሴ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አክሊሉ አለማዬሁ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ ካለው ዘርፈ ብዙ አበርክቶዎች በተጨማሪ አቅም ላነሳቸው ወገኖች በየጊዜው የሰብዓዊነትን እሴት የሚያሳድግ ድጋፍ የሚያደርግ ስለሆነ ባንኩ ከህዝቡ ጎን በመቆም የሚያከናውናቸው በጎ ተግባራት የሚያስመሰግነው መሆኑን ተናግረዋል።
ድጋፉን ያገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግራቸውን በመገንዘብ ከጎናቸው በመቆሙ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
05/09/2026
“አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድሬዳዋ ዲስትሪክት አቅም ለሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።
***********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ "አገልጋይነት እና በበጎነት" በሚል መሪ ቃል አቅም ለሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የበዓል መቀበያ የሚሆን የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናውኗል።
የባንኩ የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ በቃና እንደገለጹት፤ ባንኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 90 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ማዋሉንና ለ2019 አዲስ ዓመት ዋዜማ ደግሞ 72 ሚሊዮን ብር በመመደብ የማዕድ ማጋራት ሥራ እያከናወነ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም በድሬዳዋ ለ200 ተረጂዎች ድጋፍ ተደርጓል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ልዩ አማካሪ አቶ ዮናስ ጥግነህ እንዳሉት ባንኩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ያደረገው አስተዋጽዎ ትልቅ ማሳያና ሌሎች ተቋማትም ወደ በጎ ፈቃድ ሥራዎች እንዲመጡ በር የከፈተ ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ በክረምቱ ወቅት በበጎ ፈቃድ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ጠቅሰው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማኅበረሰቡ ያለውን አጋርነት እያሰፋ መምጣቱንና ያለው ለሌለው ማካፈል እንዳለበት በተግባር ያስተማረ መሆኑን ገልጸዋል።
05/09/2026
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስኬት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ ነው!
ከ645 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር፣ ከ707 ቢሊዮን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ፣ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እና ከ84 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ተመዝግቧል
******************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በባለቤትነት ለሚያስተዳድረው ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አቅርቧል።
የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ባንካችን በበጀት ዓመቱ በሁሉም ቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች ስኬታማ ዓመት አሳልፏል። በተለይም ሰፋፊ የብድር አማራጮችን በማቅረብ ከ645 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር የተሰጠ ሲሆን፣ 90 በመቶ የሚሆነው የባንኩ የገንዘብ እንቅስቃሴ በዲጂታል አማራጮች የተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ ከ707 ቢሊዮን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን፣ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱን እና ከ84 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ መመዝገቡን አቶ አቤ ይፋ አድርገዋል።
ባንካችን ከዚህ ስኬቱ ጎን ለጎን ለማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎችና ድጋፎች ከ309 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉም ተጠቅሷል። አቶ አቤ አክለውም በቀጣዩ በጀት ዓመት የብድር ተደራሽነትን ይበልጥ በማስፋት ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብን ወደ 832.59 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ መታቀዱን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መለከት ሳህሉ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁሉም መለኪያዎች ያሳየው ስኬት ተቋሙ በጥሩ ጤናማ አካሄድ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ እየቀጠለ ነው" ያሉት ምክትል ሥራ አስፈፃሚዋ፣ የባንኩ ጤናማ ጉዞ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጤናማነትና ጥንካሬ በተግባር የሚያሳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ባንኩ በሀገር ደረጃ ያሳየው ጥንካሬ ከውጭ ሀገራት ተመሳሳይ ዘርፍ ተቋማት ጋር ያለው ተፎካካሪነትም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ተሳተፊዎች ባንኩ በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦትና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያሳየው አፈፃፀም አመርቂ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ዕቅዶችና ይበልጥ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችንና የአቅጣጫ ምክረ-ሀሳቦችን አንስተዋል።
ለተነሱት ጥያቄዎችም በባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አማካኝነት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
ለአዲስ አመት ከሀገርዎ ጋር ኮኔክት አድርገው
ወዳጅ ዘመዶችዎን ያስደስቱ!
CBE Connect
🌼🌼 🌼🌼
በውጭ ሀገር በቀላሉ የሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት ተጠቃሚ በመሆን
በነፃ፣ በፍጥነት፣ ዳጎስ ካለ ጉርሻ ጋር ቀጥታ ወደ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ ልከው የወዳጅ ዘመዶችዎን ምርቃት ይቀበሉ!
አሁኑኑ መተግበሪያውን ስልክዎ ላይ በመጫን የሲቢኢ ኮኔክት ዋሌት ባለቤት ይሁኑ!
⬇️ ለአንድሮይድ -
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.connectethiopia&hl=en
⬇️ ለአይፎን - https://apps.apple.com/us/app/cbe-connect/id6753888802
🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት! 🌼🌼
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
05/09/2026
አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት'
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንፋስ ስልክ ዲስትሪክት የ2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 200 አቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ።
🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዕከላዊ ሪጅን ዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አንዱአለም ጌታቸው በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ባንካችን የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካማ ወገኖችን በመደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው።
ባንካችን በ2019 በጀት ዓመት ለማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አንድ መቶ ሰማንያ ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ 20ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል ።
የንፋስ ስልክ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ተመስገን ድሪባ እንደተናገሩት ባንካችን ለ2019 አዲስ ዓመት የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ብቻ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የመደበ ሲሆን፣ በዚህም በሁሉም ዲስትሪክቶቻችን አማካኝነት ከ6,600 በላይ ለሚሆኑ ወገኖቻችን ‘አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት' በሚል መሪ ቃል ማዕድ በማጋራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የፉሪ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ ዶክተር ሀላከ ዋቆ በበኩላቸው በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሉን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች እያደረገ ያለው ድጋፈ አበረታችና አርአያነት ያለው ነው።
ድጋፉን ያገኙ ወገኖችም፣ ባንኩ ችግራቸውን በመረዳት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ባንካችን ባለፉት አስር ዓመታት ብቻ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ለማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባራት ማዋሉ ይታወቃል።
🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት! 🌼🌼
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!