18/05/2020
DMLD
Daniel Mamo
18/05/2020
25/03/2020
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች እንደየአስፈላጊነቱ እና ተቋማቱ በሚያወጡት ደንብ መሰረት ከቤት ሆነው እንዲሠሩ ተወሰነ
**********
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከነገ ጀምሮ የፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ሥራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ወስኗል፤ ይህ አሠራር ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ከቤታቸው ሆነው የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች በእያንዳንዱ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አማካኝነት በሚወጣ ደንብ የሚለዩ ሲሆን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቹ ለሠራተኞቻቸው ማን ከቤት ሆኖ እንደሚሠራ የሚያስታውቁ ይሆናል።
በዚህ ወቅት ከቤታቸው ሆነው የሚሠሩ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አስተዋፅኦዋቸውን ለሚፈልጉ ሥራዎች ዝግጁ እና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት የሚወጡ መሆን ይኖርባቸዋል።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው በመላው አዲስ አበባ የሚካሄድ እንቅስቃሴን እና የትራንስፖርት ዘርፉን መጨናነቅ ለመቀነስ ታስቦ ነው።
ከጤና፣ ከደህንነት ዘርፍ እና ከኢኮኖሚ ንዑስ ኮሚቴዎች በተጨማሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ተጨማሪ ንዑስ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።
ከተጨማሪዎቹ ንዑስ ኮሚቴዎች ውስጥ የአግልሎ ማቆያ ኮሚቴ ይገኙበታል። አግልሎ የማቆያ ተቋማትን የማዘጋጀት እና አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራን በበላይነት ያስተባብራል።
የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂው ንዑስ ኮሚቴው ደግሞ ግንዛቤን ለማስጠጨበጥ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ለማስተባበር እና የተግባቦት ሥራን ለማካሄድ እንዲሁም ለስብሰባዎች የሚሆኑ የቴክኖሎጂ አማራጮችን እንደሚሠራ ተገልጿል።
13/12/2019
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Contact the business
Telephone
Website
Address
Damboya
Durame