21/08/2021
የአዲሱ ዋና መ/ቤት ህንፃ እውነታዎች!
Mobile payment services
21/08/2021
የአዲሱ ዋና መ/ቤት ህንፃ እውነታዎች!
16/07/2021
12/06/2021
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ላይ መሳተፉ ለግንባታው ዘርፍ ትልቅ ልምድ የሚያስተላልፍ መሆኑ ተገለፀ
===========
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ላይ መሳተፉ ለግንባታው ዘርፍ ትልቅ ልምድ የሚያስተላልፍ መሆኑን በዘርፉ የሚሰሩ ምሁራን ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በግንባታ ዘርፍ የማማከርና የግንባታ አስተዳደር ሥራዎችን የሚሠሩት ዶ/ር ውብሸት ዠቅአለ እንዳሉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ የዲዛይንና የግንባታ ፕሮጀክት ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማማከር ሥራ ላይ በመሳተፉ ለዩኒቨርሲቲውና ለሃገር ትልቅ አቅም መገንባት ተችሏል፡፡
ዶር ውብሸት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ የዲዛይን መረጣና ሌሎች የጥናትና ድርድር ስራዎችንም የሠሩ ሲሆን ከዋና መስሪያ ቤቱ ግንባታ ፕሮጀክት አዲስነትና ግዙፍነት የተነሳ ለፕሮጀክቱ ዋና ተቆጣጣሪና አማካሪ ለመምረጥ ፈታኝ እንደነበር አስታውሰው፣ ለዩኒቨርሲቲውና ለሃገርም ትልቅ አቅም መገንባት እንደሚቻል ታምኖበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማማከር ሥራውን እንዲሠራ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በግላቸውም በግንባታና በዲዛይን ስራዎች ላይ የተሰማሩት ዶ/ር እሸቱ ተመስገን በበኩላቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማካሪነት መሳተፉ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትና ፕሮጀክቱን በዋና ተቆጣጣሪነት እየመሩ ያሉት ዶ/ር አብርሃም አሰፋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውሳኔ ኢንስቲቲዩቱ ትልቅ አቅም እንዲገነባና ተጨባጭ ጥቅሞችን እንዲያገኝ ያደረገ ለዘርፉም ትልቅ ልምድ የሚያስተላልፍበት ነው ብለዋል፡፡
በ2007 ዓ/ም መጨረሻ ግንባታው የተጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ በአሁኑ ወቅት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ የቀሩት ሲሆን በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
01/06/2021
Enjoy telebirr promotional gifts.
Join our new Telegram channel https://t.me/telebirr to get the latest information about telebirr
24/05/2021
22/04/2021
Fegegta